አትፍረድ!
ያወቅክ ሲመስልህ የማታውቀው ብዙ ነገር አለበድሮ ጊዜ እጅግ በጣም የሚዋደዱ ደሃ ባልና ሚስት ነበሩ ፍቅራቸው በእጅጉ ያስቀና ነበር። በፍቅርና በደስታ ሲኖሩ፣ ሲኖሩ አንድ ቀን ባልየው በድንገት ታሞ ራሱን ስቶ ይወድቃል።
እናም ሚስትየው ልታሳክመው ተሸክማው ወደ ሆስፒታል ትወጣለች። ተሸክማው ስትሄድ፣ ስትሄድ ወንዝ ዳር ትደርሳለች። ሆስፒታሉ ያለው ከወንዙ ማዶ ነበረ። እንዴት ብላ ትሻገር? ድንገት ዞር ስትል አንድ አሳ አጥማጅ ጀልባው ላይ ሆኖ ታየዋለች።
እናም 'እባክህ እርዳኝ! ድሃ ነኝ! የምከፍልህ ነገር የለኝም።
ባሌ እንዳይሞትብኝ ወንዙን አሻግረኝ" ብላ ትለምነዋለች። አሳ አጥማጁም ሴቶች ሁሉ የጠሉት፣ ፍቅር የተራበ፣ ፍትዎት የተጠማ ነበርና ''አብረሽኝ ከተኛሽ ብቻ አሳግርሻለው" አላት። እሷም ምንም አማራጭ ስላልነበራት 'እሺ' ትለዋለች። የሚያደርጉትን ነገር አድርገው ያሻግራትና ባልዋን አሳክማ ታድነዋለች።
ከጥቂት ቀናት በኋላ ግን ከአሳ አጥማጁ ጋር ያደረገችው ነገር ህሊናዋን ስለረበሻት እውነቱን ለባልዋ ትነግረዋለች። ባልየውም ክፉኛ ተናዶ "ገላሽን ሸጠሽ ከምታሳክሚኝ
ብሞት ይሻለኝ ነበር" ብሎ ፈታት ይባላል።
ማናቸው ትክክል? የተሳሳተውስ ማነው? ባል፣ ሚስት
ወይስ አሳ አጥማጅ?.......
እናንተ ምን ትላላችሁ?......
መልሳችሁን comment ላይ አስቀምጡ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UC9tVBR91TfglzJDTQpwN1sg
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment