*********አሳብደውን ሲያበቁ ሀኪም ቤት ከፍተው መድሀኒት ይቸረችሩልናል፤ ራሳችንን ለታመምነው እግራችንን ይቆርጡብናል፤ ተርበናል ስንል ስለ ረሃብ አስከፊነት የሚያትት ድስኩር ይግቱናል፤ ፈረሱ ነው ቀዳሚ ስንል ጋሪው ይቀድማል ይሉናል፤ ይሁንላችሁ ከተስማማን ጋሪው ነው ስንል ፈረሱ ነው ይሉናል፤ ካሰብንበት ያድርሰን እንጂ ማንስ ቢቀድም ምን አገባን ብለን ስንተዋቸው ነውር ነው በሀገር ጉዳይ ምን አገባኝ አይባልም ይሉናል፤ ይሁን በሀገር ጉዳይ ዝም አይባልም ብለን ገና ቃል ስንተነፍስ ዝም በል! እንደ እርጎ ዝምብ በማይመለከትህ ጥልቅ አትበል ይሉናል።
በቁም የሞታችንን መርዶ እየነገሩን እንድስቅ ይኮረኩሩናል፤
ጨርቃችንን አስጥለው አሳብደው እነሱ በልካቸው አሰፍተው ለብሰው ይደምቁበታል።
የጅማዉ መንገደኛው ባለቅኔ ከድር ሰተቴ (እንደልቡ) የልቤ ሰው ❤❤
Nebil
No comments:
Post a Comment